Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የያዘችው አቋም ምስራቅ አፍሪካ ላይ ሽብርተኝነትን የሚያስፋፋ ነው ተባለ

አዲስ አበባ ፣መስከረም 4፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የያዘችው አቋም በምስራቅ አፍሪካ ሽብረተኝነትን የሚያስፋፋ አካሄድ መሆኑን የህግ ባለሙያው አቶ ውብሸት ሙላት ገለፁ።
አቶ ውብሸት ሙላት በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፥ አሜሪካ ሽብርተኝነትን በግልጽ እንደምትዋጋ ስትናገር ብትቆይም የኢትዮጵያ መንግሥት ሽብርተኛ ብሎ የፍረጀውን የህወሓት ቡድን መደገፉ በምስራቅ አፍሪካ ሽብርተኝነትን የሚያስፋፋ ነው።
አሜሪካ አሸባሪውን ህወሓት መደገፏም ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ያላትን ቁርጠኝነት ጥርጣሬ ውስጥ የሚከት ነው ያሉት የህግ ባለሙያው፥ አሜሪካ የወሰደችው አቋምም ሽብርተኝነትን ለመዋጋት የወጡ ዓለም አቀፍ ህጎችንና ስርዓቶችን የሚጥስ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ ሉዓላዊት አገር በመሆኗና በሀገሪቱም ፓርላማ የተወሰነውን የህወሓትን የሽብር ድርጊት አክብሮ መቀበል ከአሜሪካም ሆነ ከሌሎች ምዕራባውያን ሀገሮች የሚጠበቅ ኃላፊነት ነው ያሉት አቶ ውብሸት፥ ከዚህ በተቃራኒ የሚወሰድ የሽብር ቡድኑን የሚደግፍ አካሄድ አካባቢው ላይ ሽብርተኝነት እንዲነግስ በር የሚከፍት መሆኑን አመልክተዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version