Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቀነዓ ያደታ ቢሾፍቱ በማገገም ላይ የሚገኙ ቁስለኞችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር ቀነዓ ያደታ ቢሾፍቱ በማገገም ላይ የሚገኙ ቁስለኞችን ጎብኝተዋል።
እናንተ የሀገራችሁን ክብር በማስቀደም የከፈላችሁት የአካል መስእዋትነት በታሪክ መዝገብ ውስጥ ተቀምጦ ለዘላለም ታሪክ ሲዘክረው ይኖራል ብለዋል።
በህክምና ላይ የሚገኙ ቁስለኛ የሰራዊት አባላትም ለሀገራቸው ክብር የከፈሉትን ዋጋ ትልቅ ቦታ በመስጠት ሚኒስትሩ ስለጎበኟቸው ደስተኛች መሆናቸውን ተናግረዋል።
የሆስፒታሉ አዛዥ ብ/ጀ ተገኝ ለታ ከጦር ሀይሎች ኮንፕረንሲቭ ሆስፒታል ፣ ከጤና ሚኒስቴር ከአለርት ሆስፒታል እና ከሌሎችም አጋር አካላት ሙያዊ እና ቁሳዊ ድጋፍ በማግኘት ለታካሚዎቹ ተገቢ እንክብካቤ በማድረግ ሀገራዊ እና ሙያዊ ሀላፊነታቸውን እየተወጡ መሆናቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version