Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያን ለማፍረስ አሰፍስፎ የተነሳውን ኃይል በመደምሰስ አይረሴ ታሪክ እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሽብርተኛውን የጥፋት ሴራ የተገነዘበው ህዝብ በኢትዮጵያዊነት ስሜት አንድ ሆነው ታሪክ የማይረሳው ታሪክ እየሠሩ ነው ሲሉ የመከላከያ አዛዥነት እና ስታፍ ኮሌጅ አዛዥ ተወካይ ኮ/ል መላኩ እንዳወቀ ገለፁ፡፡
አሸባሪው የህወሓት ቡድን በአፋር እና በአማራ ክልል ሰርጎ በገባባቸው አካባቢዎች በንፁሃን ዜጎች ላይ የፈፀመው ኢሰብአዊ ድርጊት ከሰው ልጅ የማይጠበቅ አስነዋሪ መሆኑን የሚያረጋግጡ እና የጭካኔው ማሳያዎች መሆናቸውንም ነው የተናገሩት፡፡
የሽብር ቡድኑ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ መንዛት አብሮት የተፈጠረ መለያ ባህሪው በመሆኑ መላው ህዝባችን ለአሸባሪው የበሬ ወለደ ትርክት ጀሮውን ሳይሰጥ ከመከላከያ ሰራዊቱ እና ከፀጥታ ኃይሉ ጎን በመሰለፍ የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ኮ/ል መላኩ መጠየቃቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version