Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዝነኞቹ የባህል ሙዚቃ ተጫዋቾች በግምባር በመገኘት የጸጥታ ሀይሉን አበረታቱ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አርቲስት ሰማኸኝ በለው እና ዋኘው አሸናፊ በግምባር በመገኘት የመከላከያ ሰራዊቱን፣ ልዩ ሀይሉን፣ ፋኖ እና ሚሊሻን አበረታተዋል።ለኢትዮጵያ ክብር ሲባል በድር በገደሉ እየተዋጉ እና እየተዋደቁ ለሚገኙ ለሁሉም የሰራዊቱ አባላት ክብር እና ምስጋና ይገባል።
እኛም ከሰራዊቱ ጎን መሆናችንን ለማሳየት በጋሸና ግምባር መገኘታቸውን አርቲስት ሰመኸኝ በለው ተናግሯል።
ድምፃዊ ዋኘው አሸናፊ ደጉ የሰሜን ወሎ እና የዋግ ህዝብ በደረሰበት ግፍ እና መከራ እንዲሁም ኢ -ሰብዓዊ ጥቃት በእጅጉ ማዘኑን ገልጿል።
አርቲስቶቹ አያይዘውም ለዚህ ህዝብ ይህ አይገባውም በሰራዊቱ እና በህዝቡ አንድነት የሽብር ቡድኑን እስከ መጨረሻው እንዋጋለን ብለዋል።
በምንይችል አዘዘው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version