Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ለመከላከያ ሰራዊት በሰጠነው አገልግሎት የህሊና እርካታ አግኝተንበታል- የሃገር አቋራጭ አውቶቡስ አሽከርካሪዎች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሃገሩን ነፃነት ለማስከበርና የህዝቡን ህልውና ለማረጋገጥ ለተሰለፈው የፀጥታ ኃይል በምንሰጠው የትራንስፖርት አገልግሎት የዜግነት ድርሻችንን ስለተወጣን ደስተኞች ነን ሲሉ የሃገር አቋራጭ አውቶብስ አሽከርካሪዎች ተናገሩ።
የህውሓትን ወራሪ ኃይል ለመደምሰስ በወሎ ግንባር ለተሰለፈው የፀጥታ ኃይል የትራንስፖርት አገልግሎት በሰጡበት ወቅት ነው ይን የተናገሩት አሽከርካሪዎቹ፡፡
የማይተካውን ሕይወት እየከፈለ ትውልድ ለሚያስቀጥለው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በሙያችን በሰጠነው አገልግሎት ድካሙን በማቃለላችንና የዘመቻው ተካፋዮች በመሆናችን በምንም የህሊና እርካታ አግኝተንበታልም ነው ያሉት፡፡
ሃገር አፍራሹ የሽብር ቡድን ሙሉ በሙሉ ተደምስሶ የህዝባችን ሰላም እስከሚረጋገጥ በተሰለፍንበት ዘርፍ የህልውና ዘመቻው አካል ሆነን እንቀጥላለን ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በወሎ ግንባር የዕዝ ጭነት ትራንስፖርት ቡድን መሪ ሌተናል ኮሎኔል ዘሪሁን ሸዋየ አዲስ ኃይል በማቅረብ ሰራዊቱን ከቦታ ወደ ቦታ በማንቀሳቀስና የግዳጅ ስምሪቱን የተቀላጠፈ በማድረግ ለምናስመዘግባቸው ሁለንተናዊ ድሎች የአሽከርካሪዎቹ ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version