Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑ የሰራዊት አባላት የማዕረግ ማልበስ ስነ ስርአት ተከናወነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ለሚገኙ የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑ የሰራዊት አባላት የማዕረግ ማልበስ ስነ ስርአት ተከናወነ::
የማዕረግ እድገት ማለት ከነበርንበት ማዕረግ አንድ ደረጃ ከፍ እንዳልነው ሁሉ በአስተሳሰብና በአመለካከትም አንድ እርምጃ ወደፊት ማለትን የሚጠይቅ መሆኑን የኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት አዛዥ ኮሎኔል አዲሱ ተርፋሳ ገልፀዋል፡፡
በዚህም በስራ አፈፃጸማችሁ፣ በስነ ምግባርና በአርአያነታችሁም ሆነ በሁሉም መልኩ ከነበራችሁበት የተሻለ በመሆን መለወጥን ይጠይቃል ሲሉም አሳስበዋል፡፡
ሁሉም የማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ የሰራዊት አባላት በተለይም የእለቱ ተሿሚዎች ቀጣይ ከመንግስት እና ከተቋሙ የሚጣልባቸውን ሀላፊነት በብቃት እንደሚወጡ ሙሉ እምነታቸውን ገልፀው÷ መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንላቸው ምኞታቸውን ማስተላለፋቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version