Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የጅማ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ማበልፀጊያ ማእከል ስራ ጀመረ

አዲ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዩኒቨርሲቲው ሊከፈቱ ከታቀዱ ሶስት የጥናት ውጤቶች ማበልፀጊያ ማእከላት አንዱ የሆነው የቴክኖሎጂ ውጤቶች ማበልፀጊያ ማዕከል ሥራ መጀመሩን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል፡፡
ዛሬ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ፋካሊቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ስራ የጀመረው ይህ ማእከል÷ የተለያዩ ስልጠናዎችና የምርምር ውጤቶችም ይገኙበታል ሲሉ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ፋካልቲ ዲን ዶክተር ኤፍሬም ዋቅጅራ ለፋና ብሮድ ካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
ጅማ ዩኒቨርሲቲ ለወደፊትም ሌሎች ካምፓሶች ውስጥ መሰል ማእከላትን የመክፈት ዕቅድ እንዳለውም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ጀማል አባፊጣ ገልጸዋል፡፡
የጥናት ውጤቶች ስራ ላይ ካልዋሉ ምንም ዋጋ እንደሌላቸው የተናገሩት ዶክተር ጀማል÷ ይህን ውጤት ከገበያ ጋር ለማገናኘት ትልቅ ስራ ይሰራል ብለዋል።
በአብዱረህማን መሀመድ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version