Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በእንግሊዝ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአሸባሪው ቡድን ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮያውያን በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ጉዳት ለደረሰባቸው የወረባቦ ወረዳ ነዋሪዎች ድጋፍ አድርገዋል፡፡

በወረባቦ ወረዳ 018 ቀበሌ ድጋፍ ያደረጉት በብሪታኒያ የሚኖሩ የኢቅራዕ ኢትዮጵያውያን ማህበር አባላት ናቸው።

የድጋፉ አስተባባሪ አቶ ኡመር እንደገለጹት÷ ገንዘብ በማሰባሰብ የተደረገው ድጋፍ የምግብ ፍጆታ መሆኑን ገልጸው ጉዳቱ በሴቶችና አረጋውያን ላይ የደረሰና ልብ የሚነካ ነው ብለዋ፡፡

ድጋፋችንም ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት አስተባባሪው፡፡

የጉዳቱ ሰለባዎች በበኩላቸው÷ ድጋፉ የእለት ደራሽ በመሆኑ ያለብንን ችግር የሚፈታ ነው ብለዋል።

ጁንታው ያደረሰው ጥፋት አስከፊ መሆኑን ጠቅሰው ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና ያቀረቡት ደግሞ የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አብዱ መሀመድ ናቸው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version