Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ለአሽከርካሪዎች ዝግ የሚሆኑ መንገዶች

አዲስ አበባ፣መስከረም 16፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የመስቀል ደመራ በዓልን ምክንያት በማድረግ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ለአሽከርካሪዎች ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን አሳወቀ፡፡

በዚህም መሰረት÷

•ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒየም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር ኦሎምፒያ አደባባይ አከባቢ፤

•ከመገናኛ ፣ በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ፤

• ከቦሌ መድሃኒያለም፤ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ፤ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያ አካባቢ፤

• ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባሻ ወልዴ ችሎት ወይም ፓርላማ መብራት አካባቢ፤

• ከፒያሣ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ በቸርችር ጎዳና ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ፤

• ከተክለ ሃይማኖት በሜትሮሎጂ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት አካባቢ፤

• ከተክለ ሀይማኖት ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ የኋላ በር አካባቢ፤

• ከሲኒማ ራስ በጎላ ሚካኤል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኢምግሬሽን የኋላ በር መግቢያ፤

• ከጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ፣ ብሄራዊ ቲያትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ፤

• ከባሻ ወልዴ ችሎት በኦርማ ጋራዥ ወደፉል ውኋ መስኪድ የሚወስደው መንገድ ንግድ ማተሚያ ቤት አካባቢ፤

• ከጎፋ በቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ ወደ ለገሐር አዲሱ መንገድ የመወስደው መንገድ ቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ መስቀለኛው ላይ፤

• ከጦር ኃይሎች ፣ ልደታ ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ሜክሲኮ አደባባይ፤
• ከሳሪስ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የቀድሞ አራተኛ ክፍለጦር አካባቢ የሚዘጉ መንገዶች ሲሆኑ ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ከቀኑ 5 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ዝግ መሆኑን አሳዉቋል፡፡

ደመራው ከሚደመርበት መስቀል አደባባይ እና ከቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ወደ ስታዲዬም እንዲሁም ከሃራምቤ ሆቴል ወደ ሴንጅ ዮሴፍ የሚያቋርጠው መስቀለኛ መንገዱ ለበዓሉ በሚደረገው ዝግጅት ምክንያት ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ዝግ ተደርጓል፡፡

ከሳሪስ እና ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ከባድ ተሸከርካሪዎች መንገዱ አጎና ሲኒማ ጋር የሚዘጋ ይሆናልም ነው የተባለው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version