Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በክልሉ የመስቀል በዓል ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ትውፊቱን ጠብቆ ተከናውኗል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስቀል በዓል በሁሉም የክልላችን አካባቢዎች ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ጠብቆ በሰላም ተጠናቋል ሲሉ የአማራ ክልል መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ግዛቸው ሙሉነህ አስታወቁ፡፡
ዳይሬክተሩ የጸጥታ አካላት፣ ወጣቶችና መላ የክልሉ ሕዝብ በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ላበረከቱት አስተዋጽኦም ምስጋና አቅርበዋል።
አያይዘውም የመስቀል በዓል ጠላቶቻችን እንዳሰቡት ሳይሆን÷ በሁሉም የክልላችን አካባቢዎች ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ጠብቆ በሰላም ተጠናቅቋል ሲሉ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ለአሚኮ ገልጸዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version