Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሀዲያ ሆሳዕና የቅጣት ውሳኔ ተላለፈበት

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀዲያ ሆሳዕና የእግር ኳስ ክለብ የቅጣት ውሳኔ ተላለፈበት።

ቅጣቱ ከወልቂጤ ከተማ ጋር በነበረው ጨዋታ አንዳንድ የሀዲያ ሆሳዕና ደጋፊዎች ከስፖርታዊ ጨዋነት ውጭ ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ ከሜዳ ውጭ ከፀጥታ ሀይሎች ጋር በፈጠሩት ግርግር ምክንያት የተላለፈበት ነው ተብሏል።

በተጨማሪም የተወሰኑ ደጋፊዎች የተለያዩ ቁሳቁሶችን በመወርወራቸውና የወልቂጤ ከተማን መኪና መስታወት በመስበር ረብሻ መፍጠራቸው ለቅጣት ውሳኔው ምክንያት መሆኑ ተነግሯል።

ይህን ተከትሎም ሀዲያ ሆሳዕና በቀጣይ የሚያደርጋቸውን ሁለት ጨዋታዎች ከሜዳው ውጭ እንዲያደርግ መወሰኑን ከኢትዮ ኪክ ኦፍ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Exit mobile version