Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የእንኳን ደስ አሎት መልእክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንኳን ደስ አሎት መልእክት አስተላልፈዋል።
ከንቲባዋ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ፥ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ዓሊ ዳግም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ስለተመረጡ በራሴ በአዲስአበባ ከተማ አስተዳደርና ነዋሪዎች ስም እንኳን ደስ አለዎት እላለሁ ! ብለዋል።
መጪው ጊዜ የስኬት እንዲሁም የጀመሩትን ኢትዮጵያን ወደ ብልፅግና የማሸጋገር ራዕይ በሁለንተናዊ መልኩ የሚያሳኩበት ብሩህ ዘመን እንዲሆንልዎ ስመኝ በታላቅ አክብሮትና እምነት ነው ሲሉም አስፍረዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version