Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በጭናክሰን ወረዳ የቆላ ስንዴ ልማትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ጭናክሰን ወረዳ እየተካሄደ ያለውን የቆላ ስንዴ ልማት እንቅስቃሴን ጎበኙ።

አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሆነው እንዲያገለግሉ በድጋሜ ከተሾሙ በኋላ የመጀመሪው የሆነው ጉብኝታቸው በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ሌሎች ወረዳዎችና ከተሞች የተገነቡ የልማት ፕሮጀክቶች ምረቃና የመሠረት ድንጋይ እንደሚያስቀምጡ ይጠበቃል።

በባሌ ወረዳ በ12 ሄክታር መሬት ላይ በ36 ሚሊየን ብር የተገነባው የኢፋ ቦሩ ዋዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version