Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በደሴ ከተማ ከ 5ሺህ በላይ ጥይቶች ተይዘዋል – የደሴ ከተማ ህዝብ ሰላምና ደህንነት መምሪያ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደሴ ከተማ ባለፈው አንድ ወራት በተደረገ ጥብቅ የኬላ ፍተሻ ከ 5 ሺህ በላይ የጥይት ቀልሀዋች መያዛቸውን የደሴ ከተማ ህዝብ ሰላምና ደህንነት መምሪያ አስወቀ፡፡
የመምሪያው ሀላፊ ኢንስፔክተር ሀሰን መሀመድ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ የጸጥታ ሀይሉ ባደረገው የተቀናጀ ስራ በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበሩ ጥይቶች ተይዘዋል፡፡
የከተማዋን ሰላም ለማሰጠበቅ በኬላዎች የሚደረገው ቁጥጥር ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት ሀላፊው÷ ማህበረሰቡ እያደረገ ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
መምሪያው የከተማዋን ሰላም ለማስጠበቅ የጸጥታ ሀይሉ እያደረገ ያለውን ተግባር እንደሚደንቅ ጠቁመው÷ በመተባበር ስሜት እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ ውጤት እያሰገኘ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በከድር መሀመድ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version