አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑና በስራ አፈጻጸማቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የሰራዊት አባላት የማዕረግ ዕድገት ሰጥቷል፡፡
የማዕከሉ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ደጀኔ ፀጋዬ÷የማዕረግ ዕድገት የሰራዊት አባላቱን ግዳጅ አፈጻጸም ወደተሻለ ደረጃ ከማሸጋገሩ በላይ የሰራዊቱን የስራ ተነሳሽነት ከፍ ያደርጋል ብለዋል።
የማዕረግ ዕድገት የሚሰጠው ለተሻለ የስራ ሃላፊነት እና ለውጤታማ ግዳጅ አፈጻጸም መሆኑን የገለጹት አዛዡ÷ አባላቱ በተመደቡበት የስራ መስክ ላይ ውጤት ማምጣት እና ለሚመሩት ሰራዊት አርኣያ መሆን እንዳለባቸው ማሳሰባቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!