Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዩኒቨርሲቲው የነዳጅ ምህንድስና የትምህርት ፕሮግራም መስጠት ሊጀምር ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ትምህርት ዘመን የነዳጅ ምህንድስና (ፔትሮሊየም ኢንጅነሪንግ ) የትምህር ፕሮግራም መስጠትሊጀምር መሆኑን አስታውቋል፡፡
 
የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር በሽር አብዱላሂ ÷ በሶማሌ ክልል ካሉት የተፈጥሮ ሃብቶች መካከል አንዱ የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
ይህን የተፈጥሮ ሃብት አልምቶ ጥቅም ላይ ለማዋል የሚደረገው እንቅስቃሴ በእውቀትና በምርምር የታገዘ ለማድረግም ዩኒቨርሲቲው በተያዘው ዓመት የነዳጅ ምህንድስና የትምህርት ፕሮግራም መስጠት ይጀምራል ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version