Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ ደመቀ መኮንን ከአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አኔት ዌበር ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸው በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ሁኔታ፣ በኢትዮጵያ እና በአውሮፓ ህብረት መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ መክረዋል፡፡

አቶ ደመቀ እንደተናገሩትም ÷ ኢትዮጵያ ሁሉን አካታች የሆነ ውይይት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ለማድረግ የያዘችውን እቅድ ወደ ተግባር ለመለወጥ ያላትን ቁርጠኝነት አፅንዖት ሰጥተው ገልፀዋል፡፡

ልዩ መልዕክተኛዋ በበኩላቸው÷ መንግስት በአሁኑ ወቅት አገሪቱ ያጋጠማትን ተግዳሮቶች ለማቃለል እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀዋል።

በተጨማሪም የአውሮፓ ህብረት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማሳደግ ያለውን ፍላጎት መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version