Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ እንዳሳሰበው የአፍሪካ ህብረት አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሱዳን አሁን ላይ የተፈጠረው ወቅታዊ ሁኔታ በእጅጉ እንዳሳሰበው የአፍሪካ ህብረት አስታወቀ።
የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማሀመት፥ በሱዳን ያለው አሁናዊ ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የሚያሳየው የጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀማዶክ እና ሌሎች የአገሪቱ ሲቪል ባለስልጣናት መታሰራቸው ነው ሲሉ ጉዳዩ ከምንም በላይ እንዳሳሰባቸው አስታውቀዋል፡፡
ሊቀመንበሩ ሙሳ ፋቂ ማሀመት፥ በሲቪሉ አስተዳደር እና በወታደሩ መካከል ያሉ ጉዳዮች በፖለቲካ ውይይትና እና ህገ መንግስታዊ ማዕቀፍ በፍጥነት እንዲፈታ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ሀገሪቷን ለመታደግ እና ለዲሞክራሲያዊ ሽግግር ውይይትና መግባባት ወሳኝ ጉዳይ እንደሆነም አስምረውበታል፡፡
ሊቀመንበሩ አክለውም የፖለቲካ መሪዎች ከእስር እንዲፈቱ እና ለሰብዓዊ መብት ጥበቃ እንዲደረግ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
ምንጭ፡- የአፍሪካ ህብረት
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version