Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ህገ-ወጥ ፓስፖርት አዘጋጅተዋል የተባሉ ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ እና የኢሚግሬሽን ዜግነትና የወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ በጋራ በመሆን በሰሩት ስራ በህገ-ወጥ መንገድ ፓስፖርት ሲያዘጋጁ የተገኙ 10 የኢሚግሬሽን ሰራተኞችን በቁጥጥር ስር ማዋል መቻላቸው ተገልጿል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ህጋዊውን የፓስፖርት አሰጣጥ ሂደት ወደ ጎን በመተው፣ የፓስፖርት ባለቤቶችን ሙሉ መረጃ በመቀየር እና በአንድ ማእከል መጠናቀቅ የነበረበትን አገልግሎት ወደ ተለያዩ ቅርንጫፎች በማዘዋወር ወንጀሉን መፈፀማቸውን በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ የሙስና ወንጀሎች ዳይሬክተር ኮማንደር ታደሰ አያሌው ገልፀዋል።
ተጠርጣሪዎቹ ከደላሎች ጋር በፈጠሩት የጥቅም ትስስር በወንጀል የሚፈለጉ ግለሰቦች እና የውጭ ሀገር ዜጎችም ጭምር ፓስፖርት እንዲያገኙ ማድረጋቸውን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version