Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአየር ሃይል የደጀን አቪዬሽን ኢንዱስትሪ የማዕረግ ዕድገት ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ አየር ሃይል የደጀን አቪዬሽን ኢንዱስትሪ የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑና የተሻለ የስራ አፈፃፀም ለነበራቸው መስመራዊ መኮንኖች የማዕረግ ዕድገት ተሰጠ።
 
የኢትዮጵያ አየር ሃይል ምክትል አዛዥ ለሰው ሃብት ልማት ብ/ጄ ይታያል ገላው÷ የማዕረግ እድገት ለበለጠ ሃላፊነት መታጨት በመሆኑ ያለውን ሃገራዊ ሁኔታ በመረዳት፣ ወቅቱ የሚጠይቀውን አመራር በመስጠት ለበለጠ ተቋማዊ የለውጥ ስኬትና የግዳጅ አፈፃፀም ስኬታማነት መትጋት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
 
በኢትዮጵያ ላይ የተደቀነውን የህልውና አደጋ ሰራዊታችን በታላቅ ተጋድሎ እየቀለበሰና አኩሪ ድሎችንም እያበሰረ በሚገኝበት ሰዓት የማዕረግ እድገት ማግኘታቸው ልዩ እንደሚያደርገው ተሿሚዎች ጠቁመዋል፡፡
 
በቀጣይም ማንኛውንም መስዋትነት በመክፈል ህዝብና መንግስት የሰጡትን ተልዕኮና ግዳጅ በብቃት እንደሚወጡ መናገራቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version