Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ለሀገር መከላከያ ሰራዊት በዳንጉር ወረዳ የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር መከላከያ ሠራዊታችንን የግዳጅ አፈፃፀም የሚያከብር የድጋፍ ሰልፍ በመተከል ዞን በዳጉር ወረዳ በማንቡክ ከተማ ተካሄዷል።
የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ክንፉ፥ ኢትዮጵያን ለባዳ አሳልፎ ላለመስጠት የምታከናውኑት ተጋድሎ በማንኛው ጊዜ ከጎናችሁ ተሰልፈን ለመዋደቅ የወረዳው ነዋሪዎች ዝግጁ ነን ብለዋል።
የሀገር አለኝታና መከታ የሆነው ሰራዊታችን እናከብርሃለን ፤ ኢትዮጵያ አትፈርስም ፤ በታሪክ ሽፍታ ሀገር መርቶ አያውቅም የሚሉ መልእክቶች በድጋፍ ሰልፉ ተላልፈዋል።
ነዋሪዎቹ ፣ በድጋፍ ሰልፉ ላይ ፣ ከመቼው ጊዜ በላይ በሀገር ለሚቃጣን የውጭም ሆነ የውስጥ ጥቃት ለመቀልበስ ከሰራዊታችን ጎን ለመሰለፍ ሙሉ በሙሉ የስነ ልቦና ዝግጁነት እንዳላቸው ማረጋገጣቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version