Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኡጋንዳ ትምህርት ቤቶች በጥር ወር በድጋሚ ይከፈታሉ-ፕሬዚዳንት ሙሴቪኒ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ በኮቪድ-19 ምክንያት ተዘግተው የቆዩት የሀገሪቱ ትምህርት ቤቶች በጥር ወር በድጋሚ እንደሚከፈቱ አስታውቀዋል፡፡
 
በሀገሪቱ በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ጀምሮ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው ቆይተዋል፡፡
 
አሁን ላይም በትምህርት ቤቶች ዝቅተኛ የክትባት ስርጭት ቢኖርም በጥር ወር በድጋሚ እንደሚከፈቱ ፕሬዚዳንት ሙሴቪኒ ተናግረዋል።
 
ከትምርት ቤቶቹ በተጨማሪ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ዙሪያ የተጣሉ የኮሮና ቫይረስ ገደቦችም ማሻሻያ እንደሚደረግባቸው ነው ፕሬዚዳንቱ የገለጹት፡፡
 
በዓመቱ መገባደጃ ላይ ተጨማሪ 23 ሚሊየን ዶዝ ክትባት በጤና ጣቢያዎች መኖራቸውን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ÷ይሁን እንጂ ኡጋንዳውያን እስካሁን ለመታከም ፈቃደኞች ባለመሆናቸው ምክንያት ክተባቶችን ተደራሽ ማድረግ አልተቻለም ብለዋል፡፡
 
ስለሆነም ከክተባት አሰጣጡ ጎን ለጎን ትምህርት ቤቶችን ከመክፈት በተጨማሪ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴው በጥሩ ሁኔታ እንዲሳለጥ እናደርጋለን ነው ያሉት፡፡
 
በኡጋንዳ እስካሁን 126 ሺህ ዜጎች ቦኮሮና ቫይረስ ሲያዙ÷ 3 ሺህ 209 የሚሆኑት ዜጎች ደግሞ በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡
 
በሚኪያስ አየለ
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version