Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

መላው ኢትዮጵያዊያን በአጠረ ጊዜ የአሸባሪዉን ቡድን ግብአተ መሬት ማጠናቀቅ አለብን-ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የአዲስ አበባ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ መላው ኢትዮጵያዊያን በአንድነት የአሸባሪዉን ቡድን ግብአተ መሬት በአጭር ጊዜ ማጠናቀቅ አለብን ሲሉ ገለጹ።
ከንቲባዋ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ፥ ዛሬ በወራሪው ቡድን ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስም 20 ሚሊየን ብር የሚገመቱ ቁሳቁሶችን ባህርዳር በመገኘት አስረክበናል ብለዋል።
አሸባሪው ህወሓት በአማራ እና በአፋር ክልል ህዝብ ላይ የፈፀመው መራር ግፍና በደል ታሪክ የማይረሳዉ በመላው ኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰ አሰቃቂ ተግባር ነው ሲሉም ገልጸዋል።
ይህ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ኢትዮጵያን የማፈራረስ ከንቱ ምኞት አስፈፃሚ የሆነዉን አሸባሪውን የህወሓት ቡድን መላው ኢትዮጵያውያን በጋራ ተረባርበን በአጠረ ጊዜ መቅበር አለብንም ነው ያሉት።
ከቅያአችሁ ተፈናቅላችሁ ዛሬ በዚህ መጠለያ ጣቢያ የምትገኙ ወገኖች በሁላችን መስዕዋትነት በሚገኘው ድል ወደ አካባቢያችሁ እንደምትመለሱ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ ሲሉም ገልጸዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version