Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ቻይና የኮሮና ቫይረስን ስርጭት ለመቆጣጠር 10 ነጥብ 26 ቢሊየን ዶላር መደበች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና የኮሮና ቫይረስን ስርጭት መቆጣጠር የሚያስችል 10 ነጥብ 26 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር መመደቧን ገለጸች።

በቅርቡ በቻይና ሁቤ ግዛት ውሃን ከተማ  የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ አሁን ላይ አድማሱን በማስፋት በተለያዩ የዓለም  ሀገራት ውስጥ በመስፋፋት ላይ ይገኛል።

በዚህ መሰረትም ቫይረሱ ከቻይና ውጪ 27 በሚሆኑ የዓለም ሀገራት ውስጥ መከሰቱ ነው የተነገረው።

በአሁኑ ወቅት በቻይና በቫይረሱ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር 908 መድረሱን የሀገሪቱ በለስልጣናት አስታውቀዋል ።

በሀገሪቱ በትናንትናው ዕለት ብቻ በቫይረሱ 97 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል፤ ይህንም እስካሁን በአንድ ቀን ውስጥ ከተመዘገበው ቁጥር  ከፍተኛው ነው ተበሏል።

ከዚህ ባለፈም በበሽታው የተያዙት ሰዎች ቁጥር 40 ሺ 171 የደረሰ ሲሆን፥187 ሺህ 518 ግለሰቦች ደግሞ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው  ይገኛል።

ቫይረሱ በቻይና በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጨ መምጣቱን ተከትሎ የሀገሪቱ የገንዘብ ሚኒስቴር በሽታውን መቆጣጠር የሚያስችል 10 ነጥብ 26 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር በጀት መመደቡን ይፋ አድርጓል።

ይህም በቻይና ሁሉም ግዛቶች የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመቆጣጠር የሚደደረገውን ጥረት ማጠናከር ያስችላል ነው የተባለው።

ምንጭ፦ ሬውተርስ እና ቢቢሲ

 

Exit mobile version