Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሃገርን ለማዳን የምንሳሳለት ነፍስም ሆነ ሀብት የለንም-የቀርሳ ወረዳ ነዋሪዎች

 
 አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሽብር ቡድኖቹን ህወሓት እና ሸኔን ሀገር የማፍረስ ሴራ የሚያወግዝ ሠልፍ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ቀርሳ ወረዳ ተካሂዷል።
ሠልፈኞቹ ጁንታው ኢትዮጵያዊያነትን አይወክልም፣ ሸኔ የህወሃት ተላላኪ ነው፣ አባቶቻችን በደምና በአጥንት ያስረከቡን ሀገር ባንዳዎች አያፈርሷትም የሚሉና ሌሎችንም መፈክሮች አሰምተዋል።
የውጪ ሃይላት በኢትዮጵያ ላይ እያደረሱት ያለውን ጫና በተባበረ ክንድ ለመመከት ከመቼውም ጊዜ በላይ አንድነታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።
ጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ኢትዮጵያን ለማዳን እያደረገ ያለውን የህልውና ዘመቻ እንደሚደግፉና በገንዘብና በአይነት እያደረጉት ካለው ድጋፍ በተጨማሪ ግንባር ለመዝመት ቁርጠኝነታቸውን ገልፀዋል።
በእዮናዳብ አንዱዓለም
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
 
 
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
 
መከላከያን ይደግፉ!
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version