Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የጣለችው ማዕቀብ ሕዝብ የመረጠውን መንግሥት እውቅና ለመንፈግ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ ላይ የጣለው ማዕቀብ በሕዝብ ይሁንታ ወደ ሥልጣን የመጣውን መንግሥት እውቅና ለመንፈግ መሆኑን ዓለም ዓቀፍ የፖለቲካል ኢኮኖሚና ደህንነት ምሁራን ተናገሩ።
አሜሪካ ኢትዮጵያን በተመለከተ የምታራምደው አቋም የኢትዮጵያን ሕዝብ የሚጎዳም ነው የአፍሪካ የፖለቲካ ኢኮኖሚ ተንታኙ ፕሮፌሰር ላውረንስ ፍሪማን የተናገሩት፡፡
ይህም በሕዝብ ይሁንታ ወደ ሥልጣን የመጣውን በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራውን መንግሥት እውቅና ለመንፈግ ያለመ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡
በአንጻሩ አሜሪካ አሸባሪውን የሕወሓት ቡድን የሚነቅፍ አቋም አለማንጸባረቋንም አንስተዋል፡፡
ይህም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጉዳት መሆኑን ነው ፕሮፌሰሩ ያረጋገጡት።
አሜሪካና አንዳንድ የምዕራቡ ዓለም ሀገራት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ላይ ጭፍን ጥላቻ እያራመዱ መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡
ዓለም አቀፍ የፀጥታ ባለሙያው ፕሮፌሰር አን ፊትዝ ጄራልድ በበኩላቸው÷ አሜሪካ ኢትዮጵያ ከቀረጥ ነፃ እድል (አጎዋ) ተጠቃሚ እንዳትሆን ማገዷ ኢትዮጵያ ላይ አላስፈላጊ ጫና ለማድረግ ነው ብለዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version