Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ሁለት የጠላት ኢላማዎች በአየር ሃይል ተመቱ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በራያና ሃጂ ሜዳ (ኪሊዋ) የሚገኙ የህወሓት የሽብር ቡድን ማሰልጠኛዎች በአየር ኃይል መመታታቸውን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አስታወቀ፡፡
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ እንደተመላከተው÷ በራያ አካባቢ አረዳ ባታ የሚገኘው የህወሓት ሽብር ቡድን ማሠልጠኛ የሆነው በአየር ሃይል ተመትቷል።
በማሠልጠኛው በአሁኑ ወቅት ለሽብር ተልእኮ የተመለመሉ በርካታ ታጣቂዎች እያሠለጠኑበት እንደነበርም ተመላክቷል፡፡
በተመሳሳይ በሰሜን ወሎና አፋር አዋሳኝ ኪሊዋ ወይም ሃጂሜዳ የሚገኘው የሽብር ቡድኑ የስልጠና እና የሎጅስቲክስ ማከማቻ እንዲሁም የጠላት ተጠባባቂ ሃይል በአየር መመታቱን መግለጫው አመላክቷል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version