Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሬውተርስ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ የሚያቀርባቸው ዘገባዎች ሃሰተኛ ናቸው- መረጃ ማጣሪያ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 3 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሬውተርስ በኢትዮጵያ የጸደቀው የአስቸኳይ ገዚ አዋጅ ዜጎች የብሔር ማንነታቸውን የሚያመላክት መታወቂያ እንዲይዙ ያስገድዳል በሚል የሃሰት ዜና እያሰራጨ መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ።
 
መረጃ ማጣሪያው የሬውተርስ ዘገባ ከእውነት የራቀ እና በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተቀመጡ መመሪያዎች ውጭ መሆኑንም አስታውቋል።
 
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዜጎች የብሄርን ማንነት የማያመላክቱና ከመታወቂያ ተመጣጣኝ የሆኑ እንደ መንጃ ፈቃድ፣ የስራ ቦታ መታወቂያ እና ፓስፖርትን እንዲጠቀሙ እንደሚፈቅድም ገልጿል።
 
ከዛ ውጭ ግን መታወቂያ መያዝ ግዴታ ነው ተብሎ መዘገቡ ስህተት መሆኑንም ነው የገለጸው።
 
አያይዞም ኢትዮጵያ ካለፉት ሶስት አመታት ወዲህ በመታወቂያ ካርድ ላይ የብሔር ማንነትን ለማስወገድ እየሰራች መሆኑን ጠቁሟል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version