Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ህወሓት የሃይማኖት አባቶችን በመግደል ፋሺስታዊነቱን አረጋግጧል

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 4 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት የሃይማኖት አባቶችን በመግደል ፋሺስታዊነቱን አረጋግጧል ሲሉ የሀረሪ ክልል የሃይማኖት አባቶች ተናገሩ።
የሃይማኖት አባቶቹ ፅንፈኛው ህወሓት የዚያድ ባሬ ወራሪ ሃይል ያልሰራውን ተግባር በወገን ላይ በመፈፀም ሽብርተኝነቱን አስመስክሯል ብለዋል።
ከዚህ ባለፈም ጁንታው በትረ ስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት በሃይማኖቶች የውስጥ ጉዳይ በመግባት ሀገራዊ አንድነት እዳይመጣ ሲሰራ እንደነበር ገልፀዋል።
በመሆኑም ጁንታውና ተላላኪዎቹ ሀገርን ለማፍረስ ዕቅድ ይዘው እየሰሩት ያለውን ማንኛውም ተግባርን እንደማይቀበሉት አስታውቀዋል።
የየእምነት ተከታዮቻቸውም እነዚህን ፀረ ኢትዮጵያ አካላት በማውገዝ እንዲንቀሳቀሱና በተቻለ አቅም ሁሉ ለጀግናው የአገር መከላከያ ሠራዊት የሚያደርጉትን ድጋፍ እንደሚያጠናክሩ ጠቁመዋል።
የሀረሪ ክልል ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ አቶ ጥላሁን ዋዳራ፥ ህወሓት እኔ ያልመራኋት ኢትዮጵያ ትፍረስ በማለት እየተንቀሳቀሰ ስለሚገኝ የሃይማኖት አባቶች ህብረተሰቡን በማስተባበር አካባቢያቸውን መጠበቅ ይገባቸዋል ብለዋል።
በተለይም በአገሪቱ የታወጀውን የአስቸኳይ ግዜ አዋጅን በማክበር ህብረተሰቡ ይንቀሳቀስ ዘንድ ቤተ እምነቶች አበርክቷቸውን የላቀ እንደሆነ ገልፀዋል።
ህወሓት የእምነት ተቋማትን በማቃጠል ከኢትዮጵያዊነት እሴት ውጪ የሆነ ተግባር ማከናወኑን የገለፁት ደግሞ፥ የክልሉ ብልፅግና ፖርቲ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አብዱልጀባር መሀመድ ናቸው።
አቶ አብዱልጀባር አያይዘውም ሽብርተኛውን ቡድን ለአንድ ጊዜና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ በሚደረገው ጥረት ሁሉ የሀረሪ ክልል የሃይማኖት አባቶች ከመንግስት ጎን እንዲሰለፉ ጥሪ አቅርበዋል።
በምንያህል መለሰ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version