Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአዊ ብሔረሰብ ዞን ለመከላከያ ሰራዊት የ9 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ህዝብ የሽብር ቡድኑን ህወሓት እየተፋለሙ ለሚገኙት ለመከላከያ ሠራዊትና ሌሎች የጸጥታ ሃይሎች 9 ሚሊየን ብር ዋጋ ያላቸው የእርድ እንስሳት ድጋፍ አድርጓል።
 
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንግዳ ዳኛው እንደገለጹት ÷የዞኑ ሕዝብ በተለያዩ ግንባሮች ለተሰማሩት መከላከያ ሠራዊትና ሌሎች የጸጥታ ሃይሎች ድጋፍ አድርጓል።
 
ድጋፉ 203 ሠንጋዎች፣ 553 ፍየሎችና በጎችን ያካተተ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
 
ድጋፉ የተሰባሰበው ከወረዳዎች፣ ከከተማ አስተዳደሮች፣ ከአገው ፈረሰኞች ማህበርና ከህብረተሰቡ መሆኑን ተናግረው፤ ድጋፉ አሸባሪው ህወሃት እስከሚደመሰስ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ማመላከታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
 
የአገው ፈረሰኞች ማህበር ሊቀመንበር አለቃ ጥላዬ አየነው ማህበራቸው የአገር ህልውናን በማስከበር ላይ ለሚገኙት የጸጥታ ሃይሎች 120 በጎች መለገሱን ተናግረዋል።
 
“አገር በጠላትና በከሀዲው ቡድን ሲወረር ዝምታን የሚመርጥ አባል የለም” ያሉት ሰብሳቢው፤ የማህበሩ አባላት ዘመቻውን ለመቀላቀል ዝግጁ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል።
 
የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ቀደም ሲል ለሕልውና ዘመቻው ከ20 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን ከዞኑ የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
 
Exit mobile version