Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ አመራሮች ለመከላከያ ሰራዊት የአንድ ወር ደመወዛቸውን ሊለግሱ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በፍትህ ሚኒስቴር ለጠቅላይ ዐቃቤ ዘርፍ ተጠሪ የሆኑ የስራ ክፍል አመራሮች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚውል የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለመለገስ ቃል ገብተዋል፡፡
አመራሩ በ 8 ወር ተከፍሎ የሚያልቅ የአንድ ወር ደመወዝ ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለመለገስ ቃል መግባታቸውን የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ፍቃዱ ፀጋ ገልጸዋል፡፡
ድጋፉ ከአመራሮቹ በተጨማሪ ባለሙያዎችን በማሳተፍ ቀጣይነት እንደሚኖረውም ነው የጠቆመው፡፡
ከገንዘብ ድጋፉ በተጨማሪ ዛሬ የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፉ አመራሮች እና ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት እና በጦርነቱ ለተጎዱ ወገኖች ደም ለግሰዋል መባሉን ከቀድሞው ጠቅላይ ዐቃቢ ሕግ ፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version