Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሽብር ቡድኑ አገርን ለማፍረስ የሚሰራው የሽብር ተግባር ያረጀ ያፈጀ ነዉ -የቀድሞ ሰራዊት አባላት

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 6 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሽብር ቡድኑ ህወሃት የውሸት ፕሮፓጋንዳዎችን እየነዛ አገርን ለማፍርስ እየሄደበት ያለው አካሄድ ከ1983 እና ከዚያ በፊት ከነበረው እንቅስቃሴው የማይለይ መሆኑ የቡድኑን አዲስ ነገር የመፍጠር ችሎታ ማነስ የሚያሳይ ነው ሲሉ የቀድሞ ሰራዊት አባላት ገለጹ።
እስከ አጋዚ ክፍለ ጦር አዛዥነት ለ22 ዓመታት የቀድሞ መከላከያ ሰራዊትን ያገለገሉት እና ከፋና ብሮደካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት ሻለቃ ወንዱ ገዛኸኝ ለውጭ ሀይሎች ፈረስ የሆነው ቡድኑ ትናንትም በጋላቢዎቹ ብርቱ ድጋፍ እና በሀሰት ፕሮፓጋንዳዎች አዲስ አበባ የገባበትን ጉዞ ዛሬም እየተጓዘበት ነው ብለዋል፡፡
በ1983 ዓ.ም ስለተፈጠረውና የወቅቱ መሪ የነበሩት ኮሎኔል መንግስቱ ሀይለማሪያም አገር ጥለው እስከ መኮብለል ያደረሳቸው በአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ጦርነት ኖሮ ሳይሆን በአሜሪካዊው ጂሚ ካርተር እና ሌሎችም የቡድኑ ደጋፊዎችበተነዛው ሀሰተኛ ፕሮፓጋንዳ ምክያት ነው ያሉት ደግሞ፥ በቀድሞ ጦር እስከ ልዩ ኮማንዶ አዛዥነት አገራቸውን ለአመታት ያገለገሉት ሻምበል ይበልጣል አድማሱ ናቸው።
ሴት የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባል የሆኑት አዲስ ኪዳን አስፋው በበኩላቸው ዜጎች አካባቢያቸውን ከሰርጎገቦች ለማጥራት በንቃት መከታተል እንዳለባቸው ተናግረዋል።
አገራቸውን ከዚህ አዋራጅ እና አገር አፍራሽ ሽፍታ ቡድን ለመታደግም በተፈለጉበት ሁሉ በቁርጠኝነት ለመሳተፍ ዝግጁ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
በአፈወርቅ አለሙ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version