Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 5 ሚሊየን ብር ተያዘ

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ አርሲ ዞን በኮፈሌ ከተማ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 5 ሚሊየን ብር መያዙን የወረዳው ፖሊስ የወንጀል መከላከል ዲቪዥን አስተባባሪ ዋና ሳጅን በዳሶ ጉደታ ገለፁ፡፡

በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ብር የተያዘው ከሻሸመኔ ከተማ ወደ ነንስቦት ከተማ ሊተላለፍ ሲል በኦሮሚያ ልዩ ፖሊስና በኮፈሌ ከተማ ፖሊስ ጥምረት ነው፡፡

ብሩ ለጥፋት ተልኮ ሊውል ሲል መያዙም ታውቋል፡፡

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘም ሁለት ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በጌታቸው ሙለታ

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version