Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሩሲያ ለ “ቻይና ሚዲያ ግሩፕ” የወዳጅነት ማሳያ ነው የተባለለትን ኒሻን ሸለመች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን ÷ ለቻይና ሚዲያ ግሩፕ ፕሬዚዳንት ፣ ሼን ሃይሾንግ የወዳጅነት ማሳያ ነው የተባለለትን ኒሻን አበረከቱ፡፡

ፑቲን ÷ ኒሻኑን ያበረከቱት የብዙኃን መገናኛው በሁለቱ ሀገራት ህዝቦች መካከል ያለውን ወዳጅነት፣ ትብብር እና መግባባት ለማጠናከር በተጫወተው የላቀ ሚና መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በፈረንጆቹ በ1994 የተጀመረው ኒሻን የማበርከት ሥርዓት ሩሲያዊያንን እና የሌሎች ሀገራት ዜጎችን ከሀገሪቷ ጋር ሠላም እና ትብብር ለማጠናከር ላከናወኑት የላቀ ተግባር እንዲሁም ላሳዩት በጎነት በመሸለም ስራውን መጀመሩን ከሲጂቲ ኤን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version