Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የቀድሞ የኦሮሚያ ፖሊስ አባላት ወደ ሥራ ገበታቸው ሊመለሱ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞ የኦሮሚያ ፖሊስ አባላትና የሥራ ኃላፊዎች አጭር ሥልጠና ከወሰዱ በኋላ የኦሮሚያን ፖሊስ ለመቀላቀል ዝግጁ መሆናቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ የቀድሞ አባላቱ ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመለሱ ጥሪ አቅርቦ ነበር።

በቀረበው ጥሪ መሰረት ከበርካታ የኦሮሚያ ዞኖች ወደ ስራ ገበታቸው ለመመለስ ፍላጎት ያሳዩ አባላትና የሥራ ኃላፊዎችም በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ የአጭር ጊዜ ሥልጠና እየወሰዱ እንደሚገኙ ኮሚሽኑ አስታውቋል።

የቀድሞ አባላቱን ወደ ሥራ ገበታቸው ለመመለስ አስፈላጊው ዝግጅት ሁሉ መጠናቀቁንም ነው ኮሚሽኑ የገለጸው፡፡

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል አራርሳ መርዳሳ ÷ የቀድሞ የኦሮሚያ ፖሊስ አባላትና የሥራ ኃላፊዎች አጭር ሥልጠና እየወሰዱ በሚገኙበት ተገኝተው እንዳበረታቷቸው ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version