Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሀገሪቱ ሊከሠት የሚችለውን የምርት እጥረት ለመቅረፍ እየሰራን ነው – የሲዳማ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገሪቱ እያካሄደች ባለችው የህልውና ዘመቻ ምክንያት ሊከሰት የሚችለውን የግብርና ምርቶች እጥረት ሊቀርፍ የሚችል ስራ እየተሰራ መሆኑን ሲዳማ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ አስታወቀ፡፡
የቢሮው ሀላፊ አቶ መስፍን ቃሬ፥ ጦርነቱ እየተካሄደ በሚገኝባቸው አካባቢዎች የሚገኙ አርሶአደሮች በግንባር ጠላትን እየተፋለሙ በመሆኑ የሲዳማ አርሶ አደሮች በአመት ሦስት ጊዜ በማልማት ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ደጀን ለመሆን እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል።
በክልሉ በበጋ መስኖ ከ57 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በማልማት 13 ነጥብ 8 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማግኘት እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የክልሉ አርሶአደሮች በግንባር ጠላትን የሚፋለሙ ኢትዮጵያውያን ደጀን በመሆን የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ሊመጣ የሚችለውን ጫና ለመቀነስ በከፍተኛ የሀገር ፍቅር ስሜት እየሰሩ እንደሚገኙም ተገልጿል።
በሞሊቶ ኤሊያስ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version