Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የጠ/ሚ ዐቢይ ወደ ግንባር መዝመት መነሳሳትን ፈጥሮልናል-የሀረር ከተማ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አህመድ ወደ ግንባር ማቅናት በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መነሳሳትን እንደፈጠረላቸው የሀረር ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።
 
የጠቅላይ ሚኒስተሩን አርአያ ተከትሎ በመዝመት የሽብርተኛውን ቡድን ግብዓተ መሬት ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን እንደሚያፋጥኑት ነው ነዋሪዎቹ የገለጹት።
 
የጁንታው አመራሮች ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲኦልም ቢሆን እንጓዛለን ሲሉ የተመኙትን ህልም፥ ኢትዮጵያ ሳትፈርስ እነሱን ሲኦል በመላክ እውን እናደርግላቸዋለን ብለዋል።
 
የጠቅላይ ሚኒስተሩ በግንባር መገኘት ለሠራዊቱ የሞራል ስንቅ ሆኖ ድል እያስመዘገበ መሆኑንም አንስተዋል ነዋሪዎቹ ።
 
ወደ ግንባር ለማቅናት ከተመዘገቡት የህብረተሰቡ ክፍሎች በተጨማሪ፥ ሌሎች የከተማዋ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ከጸረ ሰላም ሃይሎች እየጠበቁ እንደሚገኙም ተናግረዋል።
 
በእዮናዳብ አንዱዓለም
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version