Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጠ/ሚ ዐቢይ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች “የ1 ሚሊየን ወደ ሀገር ቤት” ዘመቻ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 22፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች “የ1 ሚሊየን ወደ ሀገር ቤት” ዘመቻ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ አቀረቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት ጥሪ የአውሮፓውያኑን አዲስ ዓመት በኢትዮጵያ ለማክበር ይፋ የሆነውን 1 ሚሊየን ዳያስፖራ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ወደ አገር ቤት እንዲገቡ የማድረግ ጥሪን እንዲቀበሉ ጠይቀዋል፡፡

Exit mobile version