Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ታሪካዊቷ የደሴ ከተማ እና የንግድና የኢንዱስትሪ ኮሪደር የሆነችው ኮምቦልቻ ከተማ በጀግኖቹ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት ነጻ ወጡ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ታሪካዊቷ የደሴ ከተማ እና የንግድና የኢንዱስትሪ ኮሪደር የሆነችው ኮምቦልቻ ከተማ፣ በጀግኖቹ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት ነጻ ወጥተዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተመራው የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት፣ ከደሴና ኮምቦልቻ በተጨማሪ በምሥራቅ ግንባር ባቲን፣ ቀርሳን፣ ገርባንና ደጋንን ነጻ አውጥቷል።

በተጨማሪም በሐርቡ ግንባር ቃሉ ወረዳን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ አስታውቋል።

Exit mobile version