Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከተመድና ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን መሪዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 30 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው እንዳሰፈሩት፥ “በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እና ከአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ጋር ውጤታማ የስልክ ውይይት አድርጌያለሁ” ብለዋል።
“ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም ሆነ የአፍሪካ ህብረት መስራች አባል እንደ መሆኗ መጠን፣ የሀገር ሉዓላዊነት ክብርን መሰረት ያደረገ የባለብዙ ወገን ግንኙነት አራማጅ ነች” ብለዋል።
Exit mobile version