Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ህገ-ወጥ የጦር መሣሪያ አዘዋዋሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ጥር 19፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ሦስት ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎች 5 ሺህ 610 የክላሽ ጥይት ከባሕርዳር ከተማ ወደ አዲስ አበባ ለማዘዋወር ሲሞክሩ በቁጥጥር ሥር ዋሉ፡፡

ሦቱት ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎች፥  መነሻውን ከአማራ ክልል ባህርዳር ልዩ ዞን ባደረገ አይሱዙ ተሽከርካሪ ውስጥ “ሻግ” በመስራትና በውስጡ 5 ሺህ 610 የክላሽ ጥይቶችን በማስቀመጥ  ወደ አዲስ አበባ ከተማ በመግባት ለሽያጭ ሊያቀርቡ ሲሉ በተደረገ ክትትል የጦር መሳሪያውን  ጨምሮ ሦስቱም አዘዋዋሪዎች ከጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር እንዲውሉ  መደረጉን ፖሊስ አስታውቋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
Exit mobile version