ህገ-ወጥ የጦር መሣሪያ አዘዋዋሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ
አዲስ አበባ፣ጥር 19፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ሦስት ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎች 5 ሺህ 610 የክላሽ ጥይት ከባሕርዳር ከተማ ወደ አዲስ አበባ ለማዘዋወር ሲሞክሩ በቁጥጥር ሥር ዋሉ፡፡
ሦቱት ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎች፥ መነሻውን ከአማራ ክልል ባህርዳር ልዩ ዞን ባደረገ አይሱዙ ተሽከርካሪ ውስጥ “ሻግ” በመስራትና በውስጡ 5 ሺህ 610 የክላሽ ጥይቶችን በማስቀመጥ ወደ አዲስ አበባ ከተማ በመግባት ለሽያጭ ሊያቀርቡ ሲሉ በተደረገ ክትትል የጦር መሳሪያውን ጨምሮ ሦስቱም አዘዋዋሪዎች ከጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን ፖሊስ አስታውቋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ