Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ታይላንድ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለ6 ሀገራት የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባት ለገሰች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ታይላንድ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለ6 ሀገራት የሚከፋፈል 3 ነጥብ 5 ሚሊየን ብልቃጥ በላይ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባት መለገሷን አስታውቃለች፡፡
ድጋፉን ያጸደቀው የታይላንድ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጉዳይ አስተዳደር ማዕከል ቃል-አቀባይ ዶክተር ታዌስሊፕ ቪሳኑዮቲን አስታውቀዋል፡፡
ድጋፉ በዓለም ጤና ድርጅት አስተባባሪነት ለሚሰራው የክትባት ማሰባሰብ ስራ ወይም የኮቫክስ ተነሳሽነት ያላትን አጋርነት የገለጸችበት መሆኑንም ቃል-አቀባዩ ጨምረው ገልጸዋል፡፡
በድጋፍ የቀረበው የክትባቱ አይነት አስትራዜኔካ ሲሆን÷ ኢትዮጵያ፣ ማይናማር፣ ላኦስ፣ ቬትናም፣ ኔፓልና ኬንያ የድጋፉ ተጠቃሚ ይሆናሉ።
ታይላንድ ድጋፉን በቀጥታ ለየሀገራቱ እንድትሰጥ ከዓለም ጤና ድርጅት ፈቃድ ማግኘቷን የገለጹት ቃል አቀባዩ÷ ድጋፉ በቀጣይ ታይላንድ ከድርጅቱ ጋር ለመስራት ዝግጁ መሆኗን ያሳየችበት እንደሆነ መናገራቸውን ባንኮክ ፖስትን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version