Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከሁለት ዓመታት በፊት የጀመርነው የአቮካዶ ምርታማነት ጥረት ፍሬያማ መሆኑን አሳይቷል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሁለት ዓመታት በፊት የተጀመረው የአቮካዶ ምርታማነት ጥረት ፍሬያማ መሆኑን ማሳየቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለፁ።
 
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በጉዳዩ ላይ በማህበራዊ ሚዲያ የትስስር ገፆቻቸው በኩል ባስተላለፉት መልዕክት “ራሳችንን በምግብ ለመቻል፣ በስንዴ ላይ እንዳደረግነው ሁሉ በአትክልትና ፍራፍሬ ምርታማነት ላይ ዐቅማችንን ማጠናከር አለብን” ብለዋል።
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም በተለይ የአቮካዶ የወጪ ንግድ በጥቂት ዓመታት ውስጥ ከቡና የወጪ ንግድ ጋር የመስተካከል አቅም እንዳለው ነው ተናግረው የነበረው።
 
2013 መስከረም ወር ላይ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የጥራት ተቆጣጣሪ አካል ፈቃድ የተሰጠው የአቮካዶ ምርትን ወደ ተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት በመላክ የምርቱን ዓለም አቀፍ ገበያ መቀላቀሏም ይታወሳል።
Exit mobile version