አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ የተመራ የልዑካን ቡድን ነገ በጅግጅጋ በሚካሄደው ሕዝባዊ የውይይት መድረክ ላይ ለመሳተፍ ጂግጂጋ ከተማ ገብቷል።
የልዑካን ቡድኑ ጅግጅጋ ከተማ ጋራድ ዊልዋል አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ÷ በርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ እና በሌሎች የክልሉ አመራሮች አቀባበል እንደተደረገለት የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡