Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በምግብና በመሠረታዊ ሸቀጦች ራስን የመቻል ጉዞ በዘላቂነት እንዲሳካ ምርታማነት ባህል ሊሆን ይገባል- ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የተጀመረው በምግብና በመሠረታዊ ሸቀጦች ራስን የመቻል ጉዞ በዘላቂነት እንዲሳካ ምርታማነት ባህል ሊሆን ይገባል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ÷ በሀገራችን ምርታማነትን ለመጨመር የሚያስችሉ ሰፊ እድሎች አሉ ብለዋል፡፡
እምቅ የተፈጥሮ ሐብት፣ ምቹ አየር ንብረት፣ ለም መሬት፣ ሰፊ የውሃ ሃብት፣ የሰው ኃይል አለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ እነዚህን በበቂ ጥቅም ላይ ያልዋሉ ሐብቶችን በማገናኘት ምርታማነትን መጨመር እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
Exit mobile version