Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአፍሪካ ቀን ላይ ሆነን ለአህጉራዊ አንድነት ራዕይ መሳካት ቁርጠኛነታችንን እናረጋግጣለን – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “በዘንድሮው የአፍሪካ ቀን ላይ ሆነን ለአህጉራዊ አንድነት ራዕይ መሳካት ቁርጠኛነታችንን እናረጋግጣለን” አሉ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ የሚከበረውን የአፍሪካ ቀንን ምክንያት በማድረግ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸውም “አያቶቻችን የነበራቸውን ሰላማዊ፣ የተሳሰረችና የበለፀገች አፍሪካን እውን የማድረግ ራዕይን ለማሳካት ቁርጠኛ ነን” ብለዋል።
የአፍሪካ ቀን በአውሮፓውያኑ የቀን አቆጣጠር ግንቦት 25 በየዓመቱ ይከበራል።
ቀኑም የዛሬው የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ሆኖ የተመሰረተበትን ቀን መሰረት በማድረግ መከበር ጀምሯል።
Exit mobile version