Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በኮንታ ልዩ ወረዳ ጉብኝት አደረጉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የማኅበረሰብ ውይይት ለማካሄድ በኮንታ ልዩ ወረዳ ጉብኝት አድርገዋል።

በልዩ ወረዳው  በተገኙበት ወቅትም ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በኮንታ ልዩ ወረዳ የመጀመሪያ ጉብኝታቸውን ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ ኮንታ ለዘርፈ ብዙ የልማት ፕሮጀክቶች በሚሆኑ የተፈጥሮ ሀብቶች የተትረፈረፈች መሆኗን ገልጸዋል።

የኢንቨስትመንት ፍሰትን ለማበረታታት፣ የኮይሻ ግልገል ጊቤ ፕሮጀክትን አፋጥኖ በማጠናቀቅ ኃይል የማመንጨት ሥራውን ማስጀመር እንደሚገባ ጠቁመዋል።

አካባቢው ያለው ታላቅ የተፈጥሮ ሀብት፣ ኮንታን በኢንቨስትመንት ለመለወጥ እና ዘላቂ ብልጽግናን ለማስገኘት የሚያስችል አቅም አለውም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

Exit mobile version