Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአውራ አምባ ማኅበረሰብ እምነት፣ ብሔርና የፖለቲካ አመለካከት አንድ ሆነን ከመኖር እንደማያግዱን ህያው ምስክር ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 21 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) እምነት፣ ብሔርና የፖለቲካ አመለካከት አንድ ሆነን ከመኖር እንደማያግዱን የአውራ አምባ ማኅበረሰብ ህያው ምስክር ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ የአውራ አምባ ማኅበረሰብ የጾታ እኩልነት፣ የሕጻናትና የአካል ጉዳተኞች ማኅበራዊ ፍትሕ በተግባር ተፈትኖ ያየንበት ነው ብለዋል።
ለሃምሳ ዓመታት በእነዚህ ዕሴቶች ጸንቶ መኖር ድንቅ ብቻ ሳይሆን ተአምርም ነው ሲሉም አስታውቀዋል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version