Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

‘ስለ ኢትዮጵያ’ ሀገራዊ የምክክር መድረክ በጅማ ከተማ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ‘ስለ ኢትዮጵያ’ በሚል ርዕስ የተዘጋጀውና በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች የሚመክረው መድረክ በጅማ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የኢትዮጵያን ታሪክ ከ”ድሮ” እስከ “ዘንድሮ” የሚያሳይ የፎቶ አውደ-ርዕይ ተዘጋጅቶ በተሳታፊዎች ተጎብኝቷል።

“ስለ ኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ በጅማ ከተማ በሚካሄደው መድረክ የሥራ ዕድል ፈጠራን በተመለከተ ውይይት እንደሚደረግ ተገልጿል።

መሰል መርሐ-ግብር ከዚህ ቀደም በድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ጂግጂጋ፣ ሐዋሳ እና አርባምንጭ ከተሞች የተካሄደ ሲሆን በጅማ ከተማ እየተካሄደ ያለው ይህ መድረክ 6ኛው መሆኑም ተመላክቷል።

በመድረኩ ላይ የሥራና ክኅሎት ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል፣ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወሉ አብዲና ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል።

በሙክታር ጣሃ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version